አማራ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በበርካታ የባንክ የሥራ መለኪያዎች የተሻለ አፈፃጸም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

Home / Announcements / አማራ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በበርካታ የባንክ የሥራ መለኪያዎች የተሻለ አፈፃጸም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የ2024/25 በጀት ዓመት በበርካታ መለኪያዎች የተሻለ አፈፃጸም ማስመዝገቡን ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና መ/ቤት በነበረ መርሃ ግብር አስታቋል፡፡

የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በነበረው መርሃ ግብር እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ በብድር እና የውጭ ምንዛሬ ስርጭት፣ በብድር አሰባሰብ እና በዲጅታል ባንኪንግ ትግበራ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡

በዚህም መሠረት የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀ የ26 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፤ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር በ41 በመቶ በማሳደግ 2.4 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉም ነው የተገለፀው፡፡

በብድር አሰባሰብ ረገድ በዓመቱ 10.4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ236.3 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፤ በሌላ በኩል በውጭ ምንዛሬ ግኝት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የ77.5 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

በተያያዘም አማራ ባንክ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ያልተጣራ ትርፉን 1.1 ቢሊዮን ብር ማድረስ የቻለ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ70 በመቶ ዕድገት የታየበት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ24.6 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 8.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ የተቻለበት ውጤታማ አመት ማሳለፉን ባንኩ አስታውቋል። አማራ ባንክ ምንም እንኳ ከተመሠረተ ገና 3 ዓመት ብቻ ያስቆጠረ ቢሆንም ያለው አጠቃላይ ሀብት በ2024/25 በጀት ዓመት የ22 በመቶ ዕድገት በማሳየት 43.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱም ነው የታወቀው፡፡

ይህንን የባንኩን ጥረት የተረዳው የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከማኔጅመንቱ የቀረበለትን አዲስ የደመወዝ ስኬል እና ጥቅማጥቅም ጥያቄ በዝርዝር ተመልክቶ ጥያቄው ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን በማመን በሙሉ ድምጽ መፍቀዱም በዕለቱ በነበረው መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል፡፡

ባንኩ በቀጣይ የበጀት ዓመት በዋናነት በሃብት ማሰባሰብ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ የባንኩን የወደፊት ተወዳዳሪነት የሚያስቀጥሉ የዲጂታል ማስፋፋትና የደንበኞቻችንን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቋል።

አማራ ባንክ 
ከባንክ ባሻገር! 

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon