የአማራ ባንክ የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2025/26 በጀት ዕቅድ ውይይት የስራ አመራሮች ዓመታዊ ጉባዔ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ተጠናቀቀ፡፡

Home / Announcements / የአማራ ባንክ የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2025/26 በጀት ዕቅድ ውይይት የስራ አመራሮች ዓመታዊ ጉባዔ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ተጠናቀቀ፡፡

አማራ ባንክ  የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማና የ2025/26 በጀት ዓመታዊ የዕቅድ ውይይት የስራ አመራሮች ጉባዔ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ሲጠናቀቅ፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የበጀት ዓመቱን ውጤታማ በሆነ ውጤት ያጠናቀቀ  መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ውጤት ባንኩን ወደተሸለ ዕድገት ለማድረስ በተጀመረ ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ የተገኘ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አማራ ባንክ በቀጣይ 5 ዓመታት የላቀ አፈፃፀም ማስመዝገብ የሚያስችለውን ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ አጽድቆ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ በ2030 በኢትዮጵያ ከሚገኙ ምርጥ 4 ባንኮች መካከለል  አንዱ ለመሆንና እ.ኤ.አ በ2040 ከአፍሪካ ምርጥ 40 ባንኮች መካከል አንዱ ለመሆን ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት ደንበኛን ማዕከል ያደረገና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት፤ ተወዳዳሪ በመሆን ለሀገራችን ኢኮኖሚ የሚኖረውን ፋይዳ በማሳደግ የባአክሲዮኖችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈትና የዲጅታል ባንክ አማራጮችን በመዘርጋት፣ የሰራተኞችን የመፈፀም አቅም በማሳደግና የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር፣ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ቁልፍ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
ዕቅዱን ለማሳካት ሁሉም የባንኩ ሰራተኛ ከተለመደው አሰራር በመውጣት በተለየ ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ በኃላፊነትና የቡድን መንፈስ በመስራት ባንኩን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ስራ አስፈፃሚው ባንኩ በበጀት ዓመቱ ላስመዘገበው ውጤት አበርክቶ ለነበራቸው፣ ሁሉም ደንበኞች፣ የባንኩ ሰራተኞችና ባለአክሲዮኖች ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በቀጣይም አማራ ባንክ በአዲስ ምዕራፍ፣ ወደ ላቀ ዕድገት ለሚያደርገው ጉዞ የተጠናከረ አብሮነታቸውንና አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠይቀዋል፡፡

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon