አማራ ባንክ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ለነዋሪዎቹ አስረከበ፡፡

Home / Agreements / አማራ ባንክ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ለነዋሪዎቹ አስረከበ፡፡

አማራ ባንክ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ለነዋሪዎቹ አስረከበ፡፡

ባንኩ በክረምቱ ዝናብ ምክንያት ለኑሮ እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ቤቶችን ከወረዳውና ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ጋር ሆኖ በቅርበት ከለየ በኋላ እስከ 2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራና የተቸገሩ አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ እንደሚያደርግ ቃል በገባው መሠረት ታድሰው የተጠናቀቁትን ቤቶች መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማስረከብ ችሏል።

ባንኩ ገንብቶ ለአቅመ ደካሞች ያስረከባቸው ቤቶች ከባንክ አገልግሎት ባሻገር በህብረተሰቡ ዘላቂ ኑሮ መሻሻል ላይ መዋዕለ-ንዋይ በማፍሰስ ከባንክ ባሻገር የሚለውን መሪ ሃሳብ በተግባር ማሳያ እንደሆኑ የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ገልጸዋል።

እንደ ባንክ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ሥራዎች ላይ ተሳትፈን የራሱን አሻራ ማስቀመጥ አንዱ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ አማራ ባንክ እንደዚህ አይነት የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲሠራ የመጀመሪያው እንዳልሆነ እና አሁንም ወደፊትም ማኅበረሰብን የማገዝ ተግባር  አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

ቤቶቹ በፊት ከነበሩበት ለኑሮ የማይመቹ ከነበሩበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው እንደ አዲስ በመሰራታቸው ነዋሪዎቹ ተደስተው ማየታቸው የበለጠ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልጸው፣ ይህንን በጎ ተግባር አማራ ባንክ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሠራ የሚያስፈልገውን ክትትል እና እገዛ በማድረግ ለፍፃሜ እንዲበቃ በማስቻሉ የልደታ ክፍለ ከተማን እና በአጭር ጊዜ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ሂደት ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ 

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው የማኅበረሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል በሚደረገው ሂደት አማራ ባንክ ተሳታፊ ሆኖ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ በመገኘቱ አመስግነው ባንኩ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሰራ በመገኘቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም ባንኩ እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር ከልብ በመነጨ በጎ ፍላጎት በመነሳት ዝቅ ብሎ ታች ያለውን ማኅበረሰብ ለመርዳት ያደረገውን ተነሳሽነት አድንቀው ወደፊትም እንደዚህ አይነቱን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አማራ ባንከ ቤቱን ሰርቶ ያስረከባቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ቀድሞ ይኖሩበት የነበረው ቤት ቆርቆሮው የተቀደደ በመሆኑ ዝናብ የሚያስገባ፣ግድግዳው የፈረሰ፣ ነፋስና ብርድ እየገባ በጤናቸው ላይ ጉዳት ያደርስባቸው እንደነበረ አስታውሰው አማራ ባንክ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ በአጭር ጊዜ ሰርቶ ማስረከቡ ደስታ እንደፈጠረባቸውና እንዲህ ባማረ መልኩ በጥራት ገነንብቶ እና ለመኖር ምቹ አድርጎ ሶፋም ገዝቶ በአዲስ ዓመት አዲስ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ማስቻሉ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ልባዊ ምስጋናቸውን ለባንኩ አቅርበዋል።

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2025 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon