የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ማስታወቂያ ለአማራ ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ!

Home / Agreements / የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ማስታወቂያ ለአማራ ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ!

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ማስታወቂያ

ለአማራ ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ!

የአማራ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፤ የጉባዔውን አጀንዳዎችንና ተጨማሪ መረጃዎችን እሁድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም በወጡት አዲስ ዘመን እና ሪፖርተር አማርኛ ዕትም ጋዜጦች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ውድ ባለአክሲዮኖቻችን የባንካችን ጠቅላላ ጉባዔ ምልዓተ ጉባዔ መሟላት እንዲችል በዕለቱ በአካል መገኘት የማትችሉ በሚቀርባችሁ የባንካችን ቅርንጫፍ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት በመገኘት ውክልና እንድትሰጡ እያሳሰብን ውክልና የምትሰጡት ሰው በጉባዔው ተገኝቶ ሊፈርምላችሁ የሚችል መሆኑን እንድታረጋግጡና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ SBB/91/2024 መሰረት ሁሉም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የባንኩ ሠራተኞች በሙሉ ውክልና መቀበል የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡


የአማራ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ!

የአማራ ባንክ፣
ከባንክ ባሻገር!

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2025 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon