አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ለአሸናፊ ደንበኞች የተዘጋጀውን የገንዘብ ሽልማት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።

Home / Agreements / አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ለአሸናፊ ደንበኞች የተዘጋጀውን የገንዘብ ሽልማት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።

ባንካችን ላለፉት ሁለት ወራት ሲያከናውን የቆየውን በፖስ (POS) እና በኪው አር ኮድ (QR Code) አማራጮች ግብይት የሚያከናውኑ ደንበኞችን የሚያበረታታ ዘመቻ በይፋ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ለአሸናፊ ደንበኞች የተዘጋጀውን የገንዘብ ሽልማት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።
 
ዕጣ የማውጣቱ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም የባንካችን የዲጂታል ባንክ ተቀዳሚ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በፍቃዱ ቸርነትና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶችና ታዛቢዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ ተካሂዷል።
 
በወጣው ዕጣ መሰረትም 50 ሽህ ብር የሚያስገኘው ሶስት አሸናፊ የዕጣ ቁጥሮች FT25283HJHS6፤ FT252743MN3Z እና FT2526077BVP ሆኖ የወጣ ሲሆን ዕድለኞችም የባንካችን ፋሲሎ፤ ሰቆጣ እና መሪ ቅርንጫፍ ደንበኞች ሆነዋል፡፡  
 
ይህን ተከትሎ ከባንካች ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ውጪ ምንም አይነት የስልክ ጥሪ ምላሽ ባለመስጠት እንዲሁም ማንኛውም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥማችሁ ወደ 690 የደንበኞች ግንኙነት ማዕከላችን በመደወል እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2025 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon