አማራ ባንክ የካቲት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በደሴ ከተማ የኢፍጣር መርሃ- ግብር አካሄደ፡፡ በኢፍጣር መርሃ-ግብሩ የአማራ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሸሪያ አማካሪዎቸ፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የፋይናንስ ሀላፊ፣ የክፍለ ከተማ ሙስሊም አመራሮች፣ የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የሥራ አመራር አባላት፣ የደቡብ ወሎ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የሥራ አመራር አባላት፣ የደሴ ከተማ የነጋዴዎች ማህበር የሥራ አመራር አባላት፣ የደሴ ከተማ የንግድ ዘርፍ ምክር ቤት የሥራ አመራር አባላት፣ የመርሀባ ካዲም በጎ አድራጎት ድርጅት የሥራ አመራር አባላት የተገኙ ሲሆን ከኢፍጣር መርሃ-ግብሩ ባሻገር ከባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሸሪያ አማካሪዎች ጋር ውይትት አካሂደዋል፡፡ከተጋባዥ እንግዶች በተሰጠ ምስክርነትም መርሃ ግብሩ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በቅረበት ለመወያየት እድል የፈጠረ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም በባቲ ከተማ ከሚገኙ የሙስሊም የሃይማኖት መሪዎች እና ነዋሪዎች ጋር በባንኩ የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶች እና በቅርንጫፍ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከባንኩ ከፍተኛ አማራሮች፣ ሸሪያ አማካሪዎች እና ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጆች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡


