አማራ ባንክ ስልታዊ ግቦቹን ለማሳካት ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን አመራሮች በሥራ አስፈጻሚነት መመደቡን አስታወቀ።

Home / Agreements / አማራ ባንክ ስልታዊ ግቦቹን ለማሳካት ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን አመራሮች በሥራ አስፈጻሚነት መመደቡን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

አማራ ባንክ የባንኩን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካትና ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር፣ በብቃታቸውና በሥራ ልምዳቸው የተመሰከረላቸው የማኔጅመንት አባላትን በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መመደቡን ገልጿል።

ሹመቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጸደቀ ሲሆን፣ ባንኩ አዲሶቹን አመራሮች የሚቀበልበትና ከተቋሙ ነባር የሥራ መሪዎች ጋር የሚያስተዋውቅበት ደማቅ የትውውቅ መርሃ ግብር አካሂዷል።

ይህ የአመራር ምደባ የባንኩን ዕድገት ለማፋጠን፣ የአገልግሎት አቅሙን ለማሳደግና በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማጎልበት ታስቦ የተከናወነ ወሳኝ እርምጃ ነው።

በዚሁ መሠረት፣ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከነባር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በማሰባጠር፣ የባንኩን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የረጅም ጊዜ ራዕይ በብቃት ለመምራት የሚያስችል ማኔጅመንት አዋቅሯል። በዚህም አቶ ሳሙኤል ታደሰ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር እና ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ አቶ እሸቴ የማታ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ቢዝነስ ኦፊሠር፣ አቶ መንግስቱ ኃይሉ ቺፍ ኮረፖሬት ሰፖርት ሰርቪስ ኦፊሠር፣ አቶ በኃይሉ ጉልላት ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሠር እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሠሮች ሹመታቸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጸድቆ በመርሃ ግብሩ ተገኝተው ትውውቅ አድርገዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ተሿሚዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፦ “ይህ የተሰጠን ኃላፊነት ባንኩን በታማኝነትና ዘርፉ በሚፈልገው ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት እንድናገለግል የተሰጠ አደራ ነው። የባንኩን ራዕይ እና ስትራቴጂ ከዳር ለማድረስ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና ለደንበኞቻችን እና ለባለአክሲዮኖቻችን ዘላቂ ዕሴት ለመፍጠር በጋራ እንሰራለን” ብለዋል።

አማራ ባንክ ይህንን ምዕራፍ ሲጀምር፣ መላው የባንኩ ሠራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር ተባብሮ በመስራት ለባንኩ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ቦርዱ አሳስቧል።

በመሆኑም አማራ ባንክ ይህንን ወቅት ከዚህ በፊት የነበረውን መልካም አፈፃጸም በማስቀጠል አዳዲስ አሠራሮች የሚተገብርበትና በጋራ በመሥራት የባንኩን ትርፋማነት የምናረጋግጥበት መሆኑን እናምናለን ያለው ቦርዱ፤ ለባለአክሲዮኖቻችንና ለደንበኞቻችን ባንካችን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ተደራሽና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን እናረጋግጣለን ብሏል። በጠንካራ አመራር፣ በዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ደንበኞችን ማዕከል ባደረገ አሰራር በመመራት አማራ ባንክ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ  የያዘውን ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የተቻለው ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጿል።

አማራ ባንክ በጠንካራ ካፒታል የተቋቋመ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ተደራሽ በመሆን ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው ያለው ቦርዱ ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ በትጋት እየሠራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

 

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2026 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon