አማራ ባንክ የ15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ለሚገኘው ዓባይ ባንክ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላለፈ፡

Home / Announcements / አማራ ባንክ የ15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ለሚገኘው ዓባይ ባንክ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላለፈ፡

(ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም) አማራ ባንክ ዓባይ ባንክ ሥራ የጀመረበትን የ15ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ የመልካም ምኞት መልዕክቱን በዓባይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ሌሎች ምክትል ሥራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት ለባንኩ ያለውን መልካም ምኞት አስተላልፏል፡፡

ከአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የተላከውን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያደረሱት የአማራ ባንክ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አባላት እና የተለያዩ መምሪያ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

አማራ ባንክን በመወከል መልዕክትያስተላለፉት የአማራ ባንክ የህዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ የአብስራ ከበደ ሲሆኑ፣ ዓባይ ባንክ ባለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ እዚህ ደረጃ የደረሰ ባንክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ አማራ ባንክ ላቀረበው የመልካም ምኞት እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ዓባይ ባንክ ከባንኩ ምስረታ ጀምሮ አብሮ እየሠራ መቆየቱን ጠቅሰው በቀጣይም የሁለቱ ባንኮች ግንኙነት በሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

 

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon