አማራ ባንክ ከጳጉሜን 3 ቀን 2017 – ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ግብይታቸውን በፖስ እና ኪውአር ኮድ አማራጮች ያከናወኑ ዕድለኛ ደንበኞችን ሸልሟል፡፡
ባንኩ በኪውአር እና ፖስ የሚደረጉ ግብይቶችን ለማሳደግ ለሁለት ወራት ገደማ አካሂዶት በነበረው በዚህ ዘመቻ 65 ዕድለኛ ደንበኞችን ኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ በነበረ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የብሔራዊ ሎተሪ ታዛቢዎች በተገኙበት ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ዕጣው የወጣላቸው ዕድለኞች ሽልማታቸውን ታኅሣሥ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በነበረ ሥነ-ሥርዓት መረከብ ችለዋል፡፡ ሽልማቱም በዘመቻው ላይ መተገለፀው መሠረት ከብር 5 ሺህ ጀምሮ እስከ ብር 50 ሺህ ነበረ፡፡
በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ባንክ የባንኪንግ ኦፕሬሽን ተ/ዋና መኮንን የሆኑት አቶ እሸቴ የማታ ለዕድለኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ዲጂታል ባንኪንግ ጊዜን በመቆጠብ እና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ገንዘብን በቀላሉ ማንቀሳቀስ የሚያስችል አማራጭ በመሆኑ ሁሉም ሊጠቀመው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ተሸላሚ ዕድለኞች በበኩላቸው ባንኩ ቃል በገባው መሠረት ሽልማቱን በወቅቱ በመስጠቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!


