አማራ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማ ከደንበኞች፣ ከባለሀብቶችና ከባንኩ ሰራተኞች ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ ውይይት አካሄደ።

Home / Agreements / አማራ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማ ከደንበኞች፣ ከባለሀብቶችና ከባንኩ ሰራተኞች ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ ውይይት አካሄደ።

አዲስ አበባ ኢትዮጵያአማራ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማና አካባው ከሚገኙ ደንበኞች፣ ለሀብቶች፣ ባለድርሻ አካላት እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁለት ቀናት የቆየ ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ የባንኩን አገልግሎት ማሻሻል፣ ከደንበኞችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እና የጋራ ድገት አቅጣጫዎችን ለመለየት ያስቻለ ነበር ተብሏል

በውይይቱ ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ ስፈፃሚ አቶ እሸቴ የማታ ተገኝተው ተሳታፊዎች ቀረቡት ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ገንቢ ሀሳቦች ምላሽ ሰጥተዋል።

ተሳታፊዎች በተለይ በአገልግሎት ፍጥነት፣ በዲጂታል ባንክ አገልግሎቶች፣በብድር አቅርቦት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ እና ግሮች አቅርበዋል። የባንኩ አመራሮችም እነዚህን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጉዳዮች በትክክል መርምረው ተገቢ እርምጃ መውሰድ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅት የባንኩ አመራር ከደንበኞች ጋር በቅርበት መስራት እና አጋርነትን ማጠናከር የተቋሙ ዋና ቅድሚያ ትኩረት መሆኑን አስረድተዋል። ባንኩ በቀጣይም የተሻለ፣ ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በውይይቱ ወቅት የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተሳታፊዎች ተነሱ ጉዳዮች ላይ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የአገልግሎት ጥራት እና ፍጥነት ማሻሻል የባንኩ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑንየደንበኞች ጥያቄ እና ቅሬታ በፍጥነት የሚመለስ ማኔጅመንት ስርዓት ጠናከርየዲጂታል ባንክ አገልግሎቶች ማስፋፋት እና ቴክኖሎጂ መጠቀም ጠናከርለንግድ እና ለኢንቨስትመንት የሚያግዙ የፋይናንስ አሰራሮች እንዲሻሻሉ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል። ቦርዱ አክሎም ባንኩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይነት መስራት እና እምነትን በተግባር ማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የአማራ ባንክ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እሸቴ የማታ በበኩላቸው በውይይቱ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ግልጽ እና ተግባራዊ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ባንኩ ከደንበኞች እና ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደ ዋና ዓላማ መያዙን የአገልግሎት ዘርፎችን በመሻሻል የደንበኛ እርካታን ማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን የቴክኖሎጂ ልማትን በማፋጠን ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት ለማቅረብ እንደሚሰራ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ዕድሎችን ለማጎልበት የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ውይይት ባንኩ ከደንበኞቹና ከባለድርሻ አካላ ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መድረክ መሆኑ ተጠቅሷል። በአጠቃላይ፣ውይይቱ የተሳካ መሆኑንና ቀጣይ በጋራ ለመስራት የተጠናከረ መሠረት እንደፈጠረ የተገለፀ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ይህን ዓይነት ውይይት ቀጣይነት እንዲኖረው ጥሪ አቅርበዋል።

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2026 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon