አማራ ባንክ ከአስመጪዎችና ላኪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ውይይት አካሄደ።

Home / Agreements / አማራ ባንክ ከአስመጪዎችና ላኪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ውይይት አካሄደ።

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21 ቀን 2018 . አማራ ባንክ ከአስመጪዎች፣ ከላኪዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው ውይይት፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ለማድረግና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠንከር እንደሚያስችለው አስታወቀ።

ይህ መድረክ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል፣ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር እና በንግድ ዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢና አባላት፣ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ የማኔጅመንት አባላት፣ ላኪዎች፣ አስመጪዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ይህም ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሰጠውን ትኩረት ያመላከተ ሆኖ አልፏል።

የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት፤ ውይይቱ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለማጠናከርና መልካም የሆነ ግንኙነት ለማስቀጠል ቁልፍ ሚና አለው። ደንበኞቻችንን እንደ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ ስትራቴጂያዊ አጋሮቻችን እንመለከታቸዋለን። ዛሬ የተነሱ ጉዳዮች በቦርድ ደረጃ ተገምግመው ወደ ተግባር ይቀየራሉ ብለዋል።

የአማራ ባንክ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እሸቴ የማታ በበኩላቸው፤ ባንኩ ከላኪዎችና ከአስመጪዎች ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በአገልግሎት ጥራት፣ በፍጥነትና በአጠቃላይ አሰራር ላይ የሚታይ ለውጥ እንደሚያመጣ ገልጸዋል። አክለውም ባንኩ ደንበኞችን ለማዳመጥና ለመሻሻል ተግቶ የሚሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የደንበኞች ስኬት የባንኩ ስኬት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በንግድና ፋይናንስ ሂደቶች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች  የገለጹ ሲሆን፣ በዋናነት፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት፤ በብድር አቅርቦት፤ የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራት፤ በዘርፉ ያሉ እድሎችን በአግባቡ መጠቀም እና የተሻለ የደንበኞች ግንኙነት የሚሉ ኃሳቦችን አንስተዋል።

በተደረገው ውይይት ባንኩ የደንበኞቹን አስተያየት በቀጥታ እንዲሰበስብ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን እንዲለይ እና ለማሻሻል የሚሆኑ ግብዓቶችን እንዲያገኝ አስችሎታል።

 

አማራ ባንክ በውይይቱ የተነሱ ጉዳዮችን ወደ ተግባር በመቀየር፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና ከደንበኞቹ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችለው መሆኑን አረጋግጧል።

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2026 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon