(አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ) አማራ ባንክ ከሀምሌ 13 – 14፣ 2018 ዓ.ም. ሲያካሂድ የነበረውን የሥራ አመራሮች ዓመታዊ ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ።
በጉባዔው ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመምሪያ እና ዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል። ጉባኤውን የከፈቱ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበ ባንኩ በተደጋጋሚ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈም አይበገሬነቱን እያረጋገጠ እና አበረታች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀው ለውጤቱ የበኩላቸውን ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የባንኩ ተጠባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በበኩላቸው የባንኩ አመራር እና ሰራተኛ በአዲሱ በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ እንዲተጋ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በቀጣዩ በጀት ዓመት (2026/27) ሊከናወኑ በሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎችና ግቦች ላይ የሥራ መመሪያ ተቀምጧል።
የጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይ ባለፈው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


