አማራ ባንክ አዳዲስ ከፍተኛ አመራሮቹን በይፋ ተቀበለ፤ ለአመራሮቹም አጠቃላይ ገለፃ ተሰጥቷል።

Home / Agreements / አማራ ባንክ አዳዲስ ከፍተኛ አመራሮቹን በይፋ ተቀበለ፤ ለአመራሮቹም አጠቃላይ ገለፃ ተሰጥቷል።

አዲስ አበባ፦ አማራ ባንክ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸው የፀደቀላቸውን አዳዲስ ከፍተኛ የአመራር አባላት በይፋ በመቀበል ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ለመሸጋገር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባንኩ ቀደም ሲል የአመራሮቹን የትውውቅ መርሃ ግብር ቢያካሂድም፣ ተሿሚዎቹ ሁሉ በአንድ ጊዜ መገኘት ባለመቻላቸው በዛሬው ዕለት ሁሉም በተገኙበት የተሟላ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የትውውቅ መርሃ ግብር አካሂዷል። 

በመርሃ ግብሩ ላይ ለአዲሶቹ ተሿሚዎች ስለ አማራ ባንክ አጠቃላይ ገለፃ (Induction) የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም በባንኩ አመሰራረት፣ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ወቅታዊ አፈፃፀምና ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በዝርዝር የሚያስረዳ ገለፃ ተደርጓል። በተጨማሪም አዲሱ የአመራር ምደባ በባንኩ ውስጥ ያለውን የአመራር ክፍተት በመሙላት፣ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በብቃት ለመፈጸም እና የአስፈፃሚነት አቅምን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተጠቁሟል። 

በመርሃ-ግብሩ የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበ ባንኩን ለተቀላቀሉ የማኔጅመንት አባላት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ አዲስ የተቀላቀሉት የማኔጅመንት አባላት ለባንኩ አዲስ አቅም እንደሚጨምሩ በማስታወስ በቀጣይ ለባንኩ የላቀ ዕድገት ከፍተኛ ሃላፊነት ዕንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡  የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ አሁን ላለበት ደረጃ ለማድረስ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ አመስግነዋል፡፡

የአማራ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ አመራርና የምልመላና ምደባ ኮሜቴ አባል  አቶ ብርሃን ኃይሉ በሰጡት አቅጣጫም፣ ባንኩ ብቃት፣ ታማኝነት እና ውጤታማነት የሚያሳዩ አመራሮችን እንደሚፈልግ ገልጸው፤ አዲሶቹ አመራሮች የባንኩን ራዕይ ወደ ተግባር ለመቀየር ብዙ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ሌሎች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በበኩላቸው፣ ባንኩን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት ከአዲሶቹ አመራሮች ብዙ ይጠበቃል ብለዋል። 

አዲሶቹ አመራሮች በበኩላቸው፣ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ ባንኩን ወደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ እና በታማኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። አማራ ባንክ ባለፉት ጊዜያት ካስተዋወቃቸው በተጨማሪ ሶስት አዳዲስ ከፍተኛ አመራሮችን በመቀበል የአስፈፃሚ አቅሙን እያጠናከረ ሲሆን፣ ይህም ባንኩን ወደ ቀጣይ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር እንደሚያግዝ ታምኖበታል። 

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2026 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon