የአማራ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ከደቡብ ምስራቅ እና ከደቡብ ምዕራብ ዲስትሪክት እንዲሁም ከቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ጋር በባንኩ ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሄዱ።
ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ፣ ባንኩ በአሁኑ ወቅት ያለበት የሥራ አፈጻጸም እና ወደፊት ሊከናወኑ በሚገባቸው ስትራቴጂካዊ ተግባራት ላይ ጥልቅ ምክክር ተደርጓል።
የአማራ ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባንኩ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የገበያ ድርሻ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኮርፖሬት ደረጃ የሚቀረጹ ስትራቴጂዎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት በቅርንጫፍ ደረጃ በሚከናወኑ ተግባራት መታገዝ ሲችሉ መሆኑን በመጠቆም፣ በቀጣይም ባንኩን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቅርንጫፍ ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በውይይቱ ወቅት የቅርንጫፎች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ቅርንጫፎች ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።
በተጨማሪም የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በከፍተኛ አመራሩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። መድረኩ ለቀጣይ ሥራዎች አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!


