(አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም) አማራ ባንክ ከለንደኑ “ባንክ ኦፍ ቤሩት” (Bank of Beirut) ጋር በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ዙሪያ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ስኬታማ ውይይት አደረገ፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን የኮረስፖንደንት ባንክ (Correspondent Banking) ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማስፋት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡


